← ወደ ማውጫው


እኛን የሚመስል ቤት መፍጠር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ቅንጦት ነው?
ከቦታና ከቀለም ለውጥ ውጭ አብዛኞቻችን የምንኖርበት ቤት ተመሳሳይ ነው። ይህ የገንዘብ ጉዳይ ነው ወይስ የአስተሳሰብ?
ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚኖር፣ ደግሞም በሪልስቴት ዘርፍ ውስጥ ዓመታትን እንዳሳለፈ ሰው ሁሌም የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ — ከቦታና ከቀለም ለውጥ ውጭ አብዛኞቻችን የምንኖርበት ቤት ተመሳሳይ መሆኑ።
ከልጅነታችን ጀምሮ የምናውቀው ተመሳሳይነት
ወደ ልጅነታችን ብንመለስ እንኳን የምንመገብባቸው ዕቃዎች፣ ሶፋው፣ ቲቪው — የቲቪው ዳንቴል ሳይቀር — ከቤት ቤት አንድ አይነት ነበሩ።
ዛሬም ቢሆን የባለቤቱን ታሪክ፣ ፍላጎትና ስሜት የሚያንጸባርቅ ቤት የምናገኘው ልክ እንደ መስከረም ወፍ ከስንት አንዴ ነው። ብዙ ጊዜ ይህን ልምድ የምናየው ሰዓሊዎችና የፈጠራ ሰዎች ጋር ብቻ ነው።
ነገር ግን እኛስ ቤታችን ማንነታችንን እንዲገልጽ አድርገን መቅረጽ አንችልም? እንችላለን!
የገንዘብ ሳይሆን የውሳኔ ጉዳይ
ይህ ሀሳብ አብዛኛው ሰው እንደሚገምተው የገንዘብ ሳይሆን የውሳኔና የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው።
- ውድ ዕቃ መደርደር ግድ አይደለም።
- ሰፊ ካሬ ውስጥ መኖርም ግድ አይደለም።
- ባለን ቦታና አቅም ውስጥ የራሳችንን የሕይወት ዘይቤ የሚያንፀባርቅ space መፍጠር እንችላለን።
እንዴት? በቀጣይ ጽሑፍ በዝርዝር እናየዋለን።
እስከዛው ግን — እናንተስ ምን ታስባላችሁ?
የራሳችንን ማንነት የሚያንጸባርቅ ቤት አለመሥራታችን የገንዘብ እጥረት ነው ወይስ የአስተሳሰብ?
ጥያቄ አለዎት? የመጀመሪያው ንግግር ነፃ ነው — ሠላሳ ደቂቃ፣ በሚመችዎ ቋንቋ።
ቀጠሮ ይያዙ