
ማስታወቂያ አይታችሁ ብቻ ቤት ለመግዛት አትወስኑ
ቆንጆ 3D ዲዛይን፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ “የቀሩት ጥቂት ቤቶች ብቻ ናቸው!”… የሪል ስቴት ማስታወቂያ አእምሯችሁ ላይ እንዴት እንደሚሰራና ከጫናው እንዴት እንደምትወጡ፣ ከውስጥ ሰው።
ይህን የምላችሁ ማስታወቂያ የሚሰራ ሰው ሆኜ ነው። የሪል ስቴት ማርኬተሮች ብዙ ገንዘብ አውጥተው ማስታወቂያ የሚያሰሩት ወይም ለብራንዲንግ የሚጨነቁት ህንፃውን ለማሳየት ብቻ እንዳይመስላችሁ፤ አእምሯችሁን influence ለማድረግም ጭምር ነው።
ማስታወቂያው ህንፃ አያሳይም፤ እናንተን ያሳያል
ቆንጆ 3D ዲዛይን፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ በድሎት የተሞላ አኗኗር በተከሸኑ ቃላት ተቀናብሮ ስታዩ፣ አእምሯችሁ ህንፃውን ብቻ ማየት ያቆማል። ራሳችሁን እዚያ ቤት ውስጥ መሳል ይጀምራል፤ ልጆቻችሁ በዚያ ሰገነት ላይ ሲጫወቱ፣ እናንተ በዚያ ወጥ ቤት ውስጥ ቡና ስታፈሉ።
ይህ የማስታወቂያው ስህተት አይደለም፤ የማስታወቂያው ስራ ነው። ግን ማስታወቂያ የሚያሳያችሁ ምርጡን ማዕዘን ብቻ ነው፤ የሰፈሩን ትራፊክ፣ የግንባታውን የጊዜ ሰሌዳ ወይም የውሉን ዝርዝር አያሳያችሁም።
ከዚያም “ጥቂት ቤቶች ብቻ ቀርተዋል!”
ስሜታችሁ ከተያዘ በኋላ ሁለተኛው ደረጃ ይመጣል። “የቀሩት ጥቂት ቤቶች ብቻ ናቸው!”፣ “ይሄን ያህል ቅናሽ እንዳያመልጣችሁ!”፣ “ቅናሹ የሚያበቃው ዛሬ ነው!” የሚሉና FOMO (የማምለጥ ፍርሃት) የሚቀሰቅሱ ቃላቶች በስሜት እንድትወስኑ ሊገፋፏችሁ ይችላሉ።
ከጫናው ለመውጣት እነዚህን አድርጉ
- 3D ምስሉንና የሳላችሁትን ላይፍስታይል ለጊዜው ወደ ጎን አድርጉ እና ፕላኑን ተመልከቱ፦ የቤቱ ካሬ፣ የክፍሎቹ አቀማመጥ፣ የፀሐይ አቅጣጫ፣ የፓርኪንግ ሁኔታ።
- ስለ ሪል ስቴት አልሚው የቻላችሁትን ያህል አጣሩ፦ ቀድሞ ያስረከባቸው ፕሮጀክቶች፣ የካርታና የግንባታ ፈቃድ ሁኔታ፣ የቀድሞ ገዢዎች ልምድ።
- በቂ ጊዜ ወስዳችሁ ከባለሙያና ከምታምኗቸው ሰዎች ጋር ተመካከሩ። ውሉን ከመፈረማችሁ በፊት ከሕግ ባለሙያ ጋር አንብቡት።
- በራሳችሁ ጊዜ ሳይቱን ጎብኙ እና የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ አረጋግጡ፤ በሽያጭ ሰው ጉብኝት ላይ ብቻ አትተማመኑ።
ማስታወቂያ ጥሩ መነሻ ነው። ቤት ከመኖሩ ብታውቁት እንኳ ጥሩ ነው። ግን መነሻ እንጂ መደምደሚያ አይደለም። ውሳኔው በራሳችሁ ጊዜ፣ በራሳችሁ መረጃ፣ በራሳችሁ ምክንያት ይሁን።
ጥያቄ አለዎት? የመጀመሪያው ንግግር ነፃ ነው — ሠላሳ ደቂቃ፣ በሚመችዎ ቋንቋ።
ቀጠሮ ይያዙ