
አንድ ህግ የቱርክን የሪልስቴት ዘርፍ እንዴት ሙሉ በሙሉ እንደቀየረው
ርክክብ ሲዘገይ የገዢውን ኪራይ የሚከፍለው አልሚው ነው — ይህ ህግ እኛ ሀገር ቢተገበር ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?
ዛሬ ወደ ቱርክ ይዤያችሁ ልበር ነው! ቱርክ የቦስፈረስ ድልድይዋና ታዋቂ የቱሪስት መስህቦቿ ብቻ አይደሉም የሚያስደንቁት — በሪልስቴት ዘርፍ ያላት አቋምም እንዲሁ የሚገርም ነው።
ህጉ ምን ይላል?
በቱርክ አገር አንድ የሪልስቴት አልሚ በገባው ውል መሰረት ቤቱን ገንብቶ በጊዜ ካላስረከበ፣ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር የገዢውን የቤት ኪራይ በቅጣት መልክ ይከፍላል።
- ቅጣቱ የኮንትራቱ የእፎይታ ጊዜ (Grace Period) ባበቃ በማግስቱ ይጀምራል።
- ርክክቡ ከ6 ወር በላይ ከዘገየ፣ ገዢው ውሉን ሰርዞ ሙሉ ገንዘቡን ከነወለዱ የመጠየቅ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ህጉ ያመጣቸው ሦስት ትላልቅ ለውጦች
በዘርፉ ላይ ትልቅ መተማመን ፈጠረ
የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ገዢዎች በቅድመ-ግንባታ (Off-plan) ደረጃ ያሉ ቤቶችን ያለ ምንም ሥጋት እንዲገዙ አስቻለ።
ገበያውን አጣራ
በበቂ ካፒታልና እቅድ የማይሠሩ አልሚዎችን ከገበያው አስወጥቶ፣ ጠንካራና ታማኝ ገንቢዎች ብቻ እንዲቀሩ መንገዱን ጠረገ።
የግንባታ ማጠናቀቂያ ዋስትና አስገደደ
ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አልሚዎች ቢከሰሩ እንኳን ቤቱን ጨርሰው የሚያስረክቡበትን ዋስትና (Building Completion Insurance) እንዲሰጡ በማስገደድ፣ ገዢዎችን ከከፍተኛ ውጥረትና ኪሳራ ታደገ።
በአጠቃላይ ይህ አሰራር በገዢዎችና በአልሚዎች መካከል ጠንካራ አመኔታን በመገንባት የሀገሪቱን የሪልስቴት ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።
እኛ ሀገር ቢተገበርስ?
ይህ ህግ እኛ ሀገር ቢተገበር ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? አልሚዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይጀምራሉ ወይስ ገበያው ላይ ሌላ ቀውስ ይፈጠራል?
ጥያቄ አለዎት? የመጀመሪያው ንግግር ነፃ ነው — ሠላሳ ደቂቃ፣ በሚመችዎ ቋንቋ።
ቀጠሮ ይያዙ